የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ለውጥ (Regimen change)

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አዲስ የፀረ ኤች. አይ. ቪ. መድኃኒት በማስመጣት ለጤና ተቋማት በቀጥታ ከሰኔ 1/2011ዓ.ም ጀምሮ ማሠራጨት መጀመሩን የኤች. አይ. ቪ እና የወባ ግብዓት ግዥ ትንበያ ቡድን መሪ ወ/ት ፅዮን ፀጋዬ ለፈውስ ጋዜጣ ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ገለፁ፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት 2018 ባወጣው የጤና መመሪያ Nevirapine መሠረት ያደረጉ የፀረ ኤች. አይ. ቪ. መድኃኒቶች ወደ Dolutegravin 50mg መሠረት ወደ አደረጉ መድኃኒቶች መቀየር እንዳለበት እንዲሁም Efavirenz መሠረት ያደረጉ የፀረ ኤች. አይ. ቪ. መድኃኒቶች የታካሚውን ሁኔታ (suitability) ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መቀየር እዳለባቸውና የመጀመሪያ ምርጫ መድኃኒት እንዲሆንም ማስቀመጡን አስተባባሪዋ ገልፀዋል፡፡

ይህ የተሻሻለ መድኃኒት በሰውነት ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን እንደሚቀንስ፣ የሲዲ 4 ወይንም ቫይረሱን የመከላከል አቅምን እንደሚጨምርና፣ ከተለያዩ መድኃኒቶች ጋር ቢወሰድ ተቃርኖ እንደሌለውና ከቀድሞው መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቱ የቀነሰ ነው ሲሉ ወ/ት ፅዮን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ይሠጥ የነበረው የፀረ ኤች. አይ. ቪ መድኃኒት በጎንዮሽ ጉዳቱ ምክንያት ብዙ ሰዎች ያቋርጡ እንደነበረና የተሻሻለው መድኃኒት ይህን ችግር እንደሚቀርፍ አስተባባሪዋ ተናግረዋል፡፡
ለመድኃኒቱ መቀየርም ዋንኛ ምክንያት በፊት ለፀረ ኤች አይ ቪ ይሰጥ የነበረው መድኃኒት ቫይረሱን መለማመዱን የዓለም ጤና ድርጅት በጥናት አረጋግጧል ብለዋል፡፡
Dolutegravin tablet አዋቂዎችና ከ20 ኪሎ በላይ የሆኑ ሕፃናት መድኃኒቱን መውሰድ እንደሚችሉ አስተባባሪዋ አክለው ገልፀዋል፡፡
መድኃኒቱን ከ1 እስከ 3 ወር የሚገኙ ነፍሰጡር እናቶች፣ እድሜያቸው በወሊድ ክልል የሚገኝና ዘመናዊ የወሊድ መቆጣጠሪያ የማይጠቀሙ ሴቶች ላይ በቂ ጥናት ባለመደረጉና የጎንዮሽ ጉዳትም እንዳለው ስለሚታመን የተሻሻለውን መድኃኒት እንዲጠቀሙ የማይመከር መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡