የ2014ዓ.ም ለእናቶች ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ምጠና ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከጤና ሚኒስቴርና ከአጋር አካላት (GHSC-PSM) ጋር በመተባበር የ2014ዓ.ም ለእናቶች ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ምጠና ዎርክሾፕ ከግንቦት 30 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ አካሄዷል፡፡ ምክክሩ የ 2014 ምጠና እና የቀጣይ ሶሥት አመታት ከእናቶች ጤና አጠባበቅ ለምናቀርባቸው ግብአቶ እንድንተነብይ ያስችላል ያሉት በኤጀንሲው የግዥ ምጠና እና የገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ በርሄ የተቀናጀ እቅድ በማቀድ ባለድርሻ አና አጋር አካላትን በማሳተፍ ይሠራል ብለዋል።ወርክሾፑ በጤና ሚኒስቴር ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሰራ ባለው የጤና ፖሊሲ መሰረት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን ግብዓቶች ለ2014 በጀት ዓመት ግዥ ምጠና ለማካሄድ እንደሆነ የእናቶችና ህፃናት ግዥ ምጠና እና የገበያ ጥናት ባለሙያ አቶ ከፍያለው መራራ ገልፀዋል፡፡በወርክሾፑ በዋናነት ከወሊድ ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ የእናቶች ሞትን ለመቀነስ በቅድሚያ ተጠቃሽ ከሆኑት የጤና አገልግሎቶች እና ቀውሶች መካከል Antenatal care (ANC), Caesarian section, prevention of PPH, Post-Partum Hemorrhage እና Preterm Labor ይገኙበታል።በቅድመ ወሊድና በድህረ ወሊድ ወቅት የሚያጋጥሙ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በምጠናው ከተጠቀሱት መሰረታዊ መድኃኒቶች ውስጥ Calcium Gluconate 10% ml injection, Ergometrine0.25mg/ml in ml injection, Magnesium Sulfate 50% in 20ml እና Mifepristone- misoprostolecopack 200mg Tablet + 200mg,4Tablet ተጠቃሾች ናቸው።የግብዓት ምጣኔ በየዓመቱ የሚሰራ ሲሆን ካለፈው ዓመት ምጠና አንፃር የዘንድሮው ከፕሮግራሙ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈና በቂ ውይይት ተደረጎበት በመሰራቱ የተሻለ ትንበያ ውጤት እንደሚያስገኝ ታምኖበታል ሲሉ ባለሙያው አብራርቷል፡፡ አዳዲስ የህክምና አሰጣጥ ለውጦች የተደረጉ እንደሉ የተገለጸ ሲሆን ይህም ነባራዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የአሁኑ ምጠና እነኝህን ለውጦች መሰረት በማድረግ የአምናውን የመከለስ ስራ እንደሚሰራ እና የሦስት ዓመት የግዥ ትንበያ ለማዘጋጀት እንደሆነ በወርክሾፑ ላይ ተገልጿል።በተጨማሪም መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የእናቶች ግብዓት ግዥ የሚመድበውን በወቅቱ ለማሳወቅና ከተለያዩ አጋር አካላት የሚገኘውን የገንዘብ ድጋፍ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት የእቅድ ስራውን በመስራት ግብዓቶችን ግዥ በመፈፀም በወቅቱ ለተጠቃሚው እንዲቀርብ ለማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል።በወርክሾፑ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኬሞኒክስ (GHSC-PSM) ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ፣ ከመንግስተ ጤና ተቋማት፣ ከCHAI, ከጋንዲና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እንዲሁም ከኤጀንሲው ክምችትና መጋዘን አያያዝ፣ ጨረታ አስተዳደር፣ ከፕሮግራም ፋይናንስ፣ የኮንትራት ማነጅመት፣ የግዥ ትንበያና የገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ሀላፊወች ተሳትፈዋል፡፡ኤጀንሲው ከ 88 በላይ ለእናቶች ጤና አጠባበቅ የሚውሉ ግብአቶችን ያቀርባል።