የ2014ዓ.ም የህፃናትና ጨቅላ ህፃናት ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ምጠና ተካሄደ።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የ2014ዓ.ም የህፃናትና ጨቅላ ህፃናት ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ምጠና ወርክሾፕ ከግንቦት 23 እስከ 26 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል ።
ወርክሾፑ በጤና ሚኒስቴር ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሰራ ባለው የጤና ፖሊሲ መሰረት የህፃናትንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚውሉ ግብዓቶችን ለ2014 በጀት ዓመት ግዥ ምጠና ለማካሄድ እንደሆነ የኤጀንሲው የእናቶችና ህፃናት ጤና ግብዓት ግዥ ትንበያ እና የገበያ ጥናት ቡድን መሪ አቶ ፈቀደ ሽፈራው ገልፀዋል፡፡
ለህፃናትና ጨቅላ ህፃናት በዋናነት ተጠቃሽ የሆኑ ገዳይ በሽታዎች እንደ pneumonian, Diarrhe , Newborn care, Neonatal sepesis እና Local bacterial infection መሆናቸው በወርክሾፑ ላይ ተገልጿል።
ህፃናቶቹን ከበሽታ ለመከላከልና ለማከም በምጠናው ከተጠቀሱት ዋና ዋና 15 አይነት መድኃኒቶች መካከል Amoxcillin 125 እና 250mg DT, Ampicilline 250mg injection, Gentamycin-40mg/ml in 2ml-injection እና Chlorihexidine 4%Gle ይገኙበታል፡፡
የግብዓት ምጣኔ በየዓመቱ የሚሰራው ሲሆን ካለፈው ዓመት ምጠና አንፃር የሚደረጉ የህክምና ለውጦችና ነባራዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የአሁኑ ምን ለውጥ አለው የሚለውን የመከለስ ስራ እንደሚሰራ ቡድን መሪው አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ለህፃናቶች ግብዓት ግዥ የሚመድበውን በወቅቱ ለማሳወቅና ከተለያዩ አጋር አካላት የሚገኘውን የገንዘብ ድጋፍ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት የእቅድ ስራውን በመስራት ግብዓቶችን ግዥ በመፈፀም በወቅቱ ለተጠቃሚው እንዲቀርብ ለማድረግ እንደሆነ ከቃለ መጠይቁ ለመረዳትችለናል።
በወርክሾፑ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኬሞኒክስ(GHSC-PSM) ፣ከR4D፣ ከዓለም አቀፍ ጤና(WHO) ድርጅት፣ ከዘውዲቱና ከጋንዲ ሆስፒታሎች እንዲሁም ከኤጀንሲው የኮንትራት ማኔጅመንት፣ ጨረታ አስተዳደር፣ የክምችትና መጋዘን አያያዝ እና የግዥ ትንበያና የገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ተሳታፊ እንደነበሩ ቡድን መሪው ተናግረዋል።አቶ ፈቀደ አክለውም ሁሉም የባለድርሻ አካላት የግብዓት ምጠና ውጤቱን የየድርሻውን በመውሰድ በጋራ በመስራት ግዥ ሂደቱን በወቅቱ በማከናውን ህፃናቶቹን ከሞት የመከላከል ሂደቱ ላይ ሁሉም የሚጠበቅበትን ሚና መወጣት አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።በወርክሾፑ ላይ በመገኘት የበኩላቸውን አስተዋዕፆ ላበረከቱ አካላና ኤጀንሲውን በግዥ ምጠና እና በሌሎች ስራዎች ላይ ቴክኒካልና ፋናንሻያል ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙ አጋር አካላት GHSC-PSM እና R4D ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሂሩት ኃይሉ