የ2017 የዘጠኝ ወራት ሀገራዊ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ፣ የአገልግሎቱና የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዳራሽ የዘጠኝ ወራት ሀገራዊ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያና ለኢትዮጵያ ያለዉ አንድምታ፤ የማክሮ ኢኮኖሚና ሪፎርም አፈፃፀም ዉጤቶችና አዝማሚያዎች ፤ የመሰረተ ልማትና ፕሮጀክት አፈፃፀም፤ ዘላቂ ልማት ፣ ማህበራዊ አካታችነት እና ሁለንተናዊ ሉአላዊነት ለአይበገሬነት ፤ አስቻይ ሁኔታ ለዘላቂ ልማት ፣ ሰላም ዲፕሎማሲና ትብብር በሚሉና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት ተካሂዷል።
መንግስት ለነዳጅ፣ ማዳበሪያ ድጎማ የሚያደርግ ሲሆን ለዜጎች ለመድኃኒት መግዣነት የሚውል የገንዘብ ድጎማ ማድረጉ ተገልጿል ፤ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የጤናዉን ዘርፍ እንዳነቃቃዉ ተገልጿል፡፡
ሲቪል ሰርቫንቱ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚኖረዉ ሚና የላቀ ሲሆን የዉስጥ አቅምን በመጠቀም ማህበረሰባችንን በትጋት ማገልገል ይኖርብናል ያሉት ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አገልግሎቱ የጀመረዉን ዲጂታይዜሽን እንደሚደግፍ ጠቁመዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ በዋንኛነት ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን መዘርጋትና የጤና መድሕን ኢንሹራንስን ጨምሮ የጤናዉ ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሞያዎች ተገቢዉን ክፍያ እንዲያገኙ እንደሚረዳ ሚኒስትር ዲኤታዉ ገልፀዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንዳሉት በአለምአቀፍና ቀጠናዊ ደረጃ የኢትዮጵያን ተፅዕኖ መጨመር እንደሚገባ አስረድተዉ ዘላቂ ልማት ፣ ማህበራዊ አካታችነት እና ሁለንተናዊ ሉአላዊነትን በማስፋት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል።
የእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም የድንገተኛ ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚረዱ 340 አምፑላንሶች ድጋፍ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤን በመጠቀም የወባ ስርጭትን ለመግታት የተደረገዉ ዘመቻ አመርቂ እንደሆነም ገልፀዋል።
የዉይይቱ ተሳታፊዎችም ተቋማዊ አደረጃጀት ላይ እና ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ባለፉት 9 ወራት በጤናዉ ዘርፍ ላይ ባመጣዉ ተጨባጭ ለዉጥ ዙሪያ ሀሳባቸዉን ሰተዉ ህብረተሰቡን ለማገልገል ያላቸዉን ቁርጠኝነት አንፀባርቀዋል። የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እና ምርታማነት እንዲሁም ተወዳዳሪነት እንዲኖር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ሪፓርቱ ያመላክታል።
