ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የግሎባል አልያንስ ቫክሲን ኢኒሼቲቭ(GAVI) ዋና ሥራ አስኪያጅ በክትባት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በአዳማ ጎበኙ፡፡

October 8, 2022Magazine
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዲሁም የጋቪ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሲዝ ብርክሌይ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በአዳማ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ በመገኘት በክትባትና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጎብኝተዋል።
የጉብኝቱ ዓላማ ከክትባት መድኃኒት ስርጭትና ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ከጋቪ በተደረጉ ድጋፎች የተመዘገብ ስኬቶችን እና ያሉ ተግዳሮች ላይ በመወያየት በቀጣይ የጤና ስርዓቱን ለማሻሻልና ለማጠናከር የሚያግዙ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል።
በዕለቱ ጋቪ(GAVI) በጤናው ሴክተር በክትባት መድኃኒትና ተያያዥ ግብዓቶች ዙሪያ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅኦ የምስጋና ስጦታ ተበርክቷል።
ጋቪ(GAVI) ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት ስርጭት ጨምሮ በኮቪድ 19 የክትባት ስርጭት ዙሪያ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
ጎብኝዎቹ በአዳማ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ያለውን የክትባት አቅርቦት፣ ስርጭትና አያያዝ በተመለከተ በቀረበ ሪፓርት ላይ ውይይት በማድረግ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።