1.8 ሚሊዮን ከረጢት Normal Saline የተባለ ነብስ አድን መድኃኒት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለጤና ተቋማት እየተሰራጨ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በጤና ተቋማት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን በሰውነታቸው ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮች ለመተካት የሚረዳ Normal Saline/NS/ የተባለ ነብስ አድን ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለጤና ተቋማት እየተሰራጨ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ገለጸ፡፡
ከህንድ ሀገር እየገባ እና እየተሰራጨ ያለው ብዛቱ 80 ኮንቴነር በላይ የሆነ 1 .8 ሚሊዮን ከረጢት ባለ 1ሺ ሚሊ ሊትር መሆኑን ለቀጣይ ሶስት ወራት የሚሆን ፍጆታ የሚያገለግል መሆኑን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል በአብዛኛውን ፍጆታ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርቱ የሚቀርብ አሠራር መኖሩን አስታውሠው ፣የሀገር ውስጥ አቅራቢዎች እንዲያቀርቡ ጥረት ቢደረግም በኮሮና ጫና፣ በጥሬ እቃ መወደድ እና የሎጀስቲክስ ተግዳሮቶች ጋር ተያይዞ ማቅረብ ባለመቻላቸው በእኛ በኩል የአቅርቦት መቆራረጥ እንዳይከሰት በውጭ ሀገር አቅራቢ እንዲቀርብ ተደርጓል ብለዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ ምርቱን ከአገር ውጭ እና ውስጥ አቅራቢዎች ለማቅረብ የ 6 ሚሊዮን ከረጢት ግዥ ለመፈጸም ዓለም አቀፍ ጨረታ አየር ላይ ነው ብለዋል፡፡ ይህም በመሆኑ ለቀጣይ አንድ አመት አስተማማኝ አቅርቦት እንዲኖር ከወዲሁ እየተሰራ ነው በማለት ሀላፊው አብራርተዋል፡፡እንደ አቶ ሰለሞን ገለፃ ህይወት አድን እና መሠረታዊ የህክም ግብአቶች እጥረት እንዳይከሰት በተለይም ለስኳር ህሙማን የሚውለው ኢንሱሊንን ጨምሮ ለደም ግፊት፣ለሥነ አዕምሮ እና ከዚህ ቀደም የአቅርቦት እጥረት ይስተዋልበት የነበረውን የህክምና የእጅ ጓንቶች ጨምሮ አስተማማኝ ክምችት እንድኖር የተሠራ ሲሆን ከውጭ ተገስተው በቀጥታ ለጤና ተቋማት የተሠራጩ መሆኑን ተናግረዋል ።ለአገር ውስጥ መድኃኒትና አምራቾች ትኩረት በመስጠት የአገልግሎት ተቋሙ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ነው ሀላፊው ያብራሩት፡፡
አወል ሀሰን