” ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ለተቋማዊ ለዉጥ” በሚል መሪ ቃል አገልግሎቱ ክንዉኖቹን ገመገመ
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በተገኙበት የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮችና አስተባባሪዎች ተቋሙ እየሰጠ ያለዉን የአገልግሎት ጥራት ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ገምግመዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ የተሻሻሉ መመሪያዎችን በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት ፤ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት ስርዓቱን ማሳደግ ፤ የህብረተሰቡን የህክምና ግብዓት ጥያቄ በበቂ ደረጃ መልስ መስጠት እንደሚገባና ብቃት ያለዉ ተወዳዳሪ ተቋም መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።
አገልግሎቱ የመድኃኒት አቅርቦቱን ለማሳለጥ ከክልልና ዞን ሃላፊዎች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሆነ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ጠቁመዉ ዉል የተገባለት የአቅርቦት ስርዓት (Committed Demand) ተፈፃሚነት እንዲኖረዉ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠዉ ፤ የለዉጥ ስራዎችን አጠናክሮ መሄድ እንደሚያስፈልግ ፤ የኦዲት ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ በመግለፅ ሁሉም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በትጋት ህብረተሰቡን ማገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ተቋማዊ ግንባታዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፤ የተናበበ የህክምና ግብዓት ስርጭት እንደሚያስፈልግ፤ የሰዉ ሃይል ግንባታዉን ማጠናከር ፤ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የለዉጥ ስራዎችን ከዳር ማድረስ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨