የተጀመረዉ መዋቅራዊ ሪፎርም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አገልግሎቱ የለዉጥ ስራዎቹን በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ ከሚያዝያ 23_25/2017 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ታደሌ ቡርካ በአገልግሎቱ የተጀመሩ መዋቅራዊ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሣሠቡ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የህዝቡን የመድኃኒት አቅርቦት ጥያቄ ፈጣን እና አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲመልስ የአገልጋይነት እርካታን ለማምጣት የአመራር ሪፎርሙ የህዝብን ጥያቄ የሚመልስ ሆኖ የራስን አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባና፤ ብልሃት፣ ቅንጅት እንዲሁም ንቃት ከሁሉም የተቋሙ አመራሮች እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
አክለውም በሚሠሩ ስራዎች ቋሚ ኮሚቴው የበኩሉን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረው፤ የተጀመረዉን የመዋቅር ሪፎርም ለማጠናከር ቋሚ ኮሚቴዉ የደንበኞችን እርካታ ከፍ ለማድረግ ከአገልግሎቱ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሆነ ዶ/ር ታደሴ ተናግረዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ቋሚ ኮሚቴዉ ተቋሙ የጀመራቸዉን የሪፎርም ስራዎች እየደገፈ መሆኑን ገልፀው የላቀ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ ክፍተቶችን በማረም የተሳለጠ አገልግሎት ሰጪነት እስኪረጋገጥና ዜጎች በቂ የሆነ የህክምና ግብዓት ግልጋሎት እስኪያገኙ ድረስ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ትብብራቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
#ማገልገል ክብር ነው
