ከነሐሴ 8-10 /2011ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ኤጀንሲው ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እንደሚያካሒድ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቃልኪዳን ላቀው ለዝግጅት ክፍሉ ተናገሩ፡፡ በምክክር መድረክ ላይ ከለጋሽ አካላት፣ ከመድኃኒት አቅራቢዎች፣ ከኤጀንሲው ደንበኞችና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር የመድኃኒት አቅርቦት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ሰኔ 11 ቀን በነበራቸው ቃለ መጠይቅ አስታውቀዋል፡፡ በመድረኩ ኤጀንሲው እየተገበራቸው ባሉ የልህቀት ማዕከል፣ […]