ኤጀንሲው ባለፋት 2 ወራት ከ550 በላይ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማንሣቱን የኤጀንሲው የመድኃኒት ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ አጋር ተስፋዬ አስታወቁ፡፡ መድኃኒቶቹ ለኤች.አይ.ቪ፣ ለሆድ ሕመም፣ ለኢንፌክሽን፣ ለስነተዋልዶ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች እንደሆኑ ወ/ሮ አጋር አብራርተዋል፡፡ ወ/ሮ አጋር ከ25 ዓይነት በላይ መድኃኒቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ በማውጣት በተለያዩ ቅርንጫፎችና በዋናው […]