የተለያዩ የመንግሥት እና የግል ሚዲያ አካላት ህዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የሐዋሣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ መጋዘን እና የመድኃኒት ማክሠሚያ/ኢንሲኔሬተር ጉብኝት አካሄዱ፡፡ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሠ ቅርንጫፉ ስለሚሠጣቸው አጠቃላይ አገልግሎቶች ለተሣታፊዎቹ ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን ለ505 የጤና ተቋማት ቅርንጫፉ አገልግሎት እንደሚሠጥ አስረድተዋል፡፡ የሐዋሣ ቅርንጫፍ 4500 ሜትር ኪዩብ የመድኃኒት ማከማቻ እንዳለው እና 3090 የመድኃኒት ማስቀመጫ ቦታ እንዳለው […]