የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በመድኃኒት ጥራት ላይ ለሚነሡ ችግሮች የቅሬታ መቀበያ መንገዶችና የመፍትሔ አሰጣጥ አሠራሮች ተዘጋጅተው እየተሰራባቸው እንደሚገኝ የጥራት ቁጥጥርና ክትትል አስተባባሪ አቶ ታደሰ አየለ ተናግረዋል፡፡ አስተባባሪው ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት ከደንበኞች የሚነሱትን የመድኃኒት ጥራት ችግሮች ቅሬታ ለመቀበል ሦስት መንገዶች ተዘጋጅተው ቅሬታቸውን በመቀበል ላይ እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ የቅሬታ መቀበያ መንገዶቹ 8772 ነጻ የስልክ ጥሪ መቀበያ […]