የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ3.1 ሚሊየን የወባ መከላከያ አጎበሮች ውስጥ ቀሪ 1.6 ሚሊየን ለ2 ክልሎች ስርጭት መጀመሩን የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭትና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሕመድ ከድር ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለፁ፡፡ ዳይሬክተሩ እንደገለጹት እነዚህ እየተሰራጩ ያሉት የወባ መከላከያ አጎበሮች ጤና ሚኒስቴር በላከው የስርጭት እቅድ መሰረት ለጋምቤላ እና ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሚገኙ […]