የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከGlobal fund ጋር በመተባበር 2.8 ሚሊየን የወባ መከላከያ አጎበሮችን ሊያሠራጭ መሆኑን የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭትና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው በቀለ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡ አጎበሮቹ በደቡብ እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ 72 ወረዳዎች እንደሚሠራጩ አቶ ሽፈራው አስታውቀው ስርጭቱ የሚካሄድባቸው ዞኖችም ሲዳማ፣ ከንባታ ጠንባሮ፣ ጉራጌ፣ ሃድያ፣ ከፋ፣ዳውሮ፣ ሸካ፣ […]