የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2012 በጀት ዓመት ለጤና ተቋማት በዱቤ ከሸጠው የሕክምና መሣሪያና መድኃኒቶች ውስጥ ከ1.3 ቢልየን ብር በላይ መሠብሠቡን የእቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ፀጋ ሠኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም.ገለፁ፡፡ ኤጀንሲው በ2012 በጀት ዓመት 1.9 ቢሊዮን ብር ወጪ ያላቸው መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በዱቤ ሽያጭ አካሂዶ ከ1.3 ቢልየን ብር በላይ መሠብሠቡን ዳይሬክተሩ […]