የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 18 የኬሚስትሪ ማሽኖችን ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ ስርጭት እያካሄደ መሆኑን የክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ ሚዛን ገ/ዮሐንስ አስታወቁ፡፡ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹ በኦሮምያ፣ አማራ እና ደቡብ ክልሎች ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት ከግንቦት ወር ጀምሮ መሠራጨቱን ባለሙያዋ አስረድተዋል፡፡ የኬሚስትሪ ማሽኖቹ ለስኳር፣ ለጉበት፣ ለኩላሊት እና ሌሎች በሽታዎች መመርመሪያነት የሚያገለግል ሲሆን ታካሚዎችን ከአላስፈላጊ ወጪ ይታደጋል፡፡