የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የአዳማ ፕሮጀክት ለፅኑ ህሙማን መተንፈሻነት አገልግሉት የሚሰጡ 180 መካኒካል ቬንትሌተሮችን ከመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እያሰራጨ መሆኑን የአዳማ ማዕከላዊ የህክምና መሳሪያዎች መጋዘን ቡድን መሪ አቶ ደበበ ገበየሁ ገለፁ። ስርጭቱም በአዳማ ፕሮጀክት አማካኝነት ለሚኒሊየም አዳራሽ የኮቨድ19 ህክምና ማዕከል ፣ ለየካ ኮተቤ ፣ ለፊልድ የኮቨድ19 ህክምና ማዕከል ሆስፒታል፣ ለጴጥሮስ፣ ለጳውሎስና ለአቤት ሆስፒታሎች […]