የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትርና የአገልግሎቱ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አህመድ ሺዴ እንዳሉት ተቋማዊ ሪፎርሞች ከሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ጋር የተናበቡ መሆን እንዳለባቸዉ ገልፀዉ ፤ አገልግሎቱም ስትራቴጃዊ እቅዶቹን ከሀገራዊ ሪፎርሙ ጋር የተጣጣመ ማድረግ እንዳለበት ገልፀዋል። በተጨማሪም የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አቅራቢዎችም የማምረት አቅማቸዉ እያደገ መምጣቱ ጥሩ ቢሆንም ገበያዉ ላይ ተወዳዳሪ መሆን እንዳለባቸዉ የቦርድ ሰብሳቢዉ ተናግረዋል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር […]