6ኛው የፋርማሲስቶች ቀን በአዳማ ከተማ ተከበረ

December 17, 2019Uncategorized @am
በአለም ለዘጠነኛ ጊዜ የተከበረው የፋርማሲስቶች ቀን በአዳማ ከተማ በኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበርና በዳኖን ኑትሪካ አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ ህዳር 25 ፈዋሽ መድኃኒቶች ለሁሉም “Safe and Effective Medicine for ALL” በሚል መርህ በሀገራችን ለስድስተኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡
በዕለቱ የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ፋርማኮሎጂሰት ዶ/ር ወርቁ በዳኔ “የፋርማሲ ሳይንስ ከየት ወዴት“ በሚልና በጤናው ሴክተር የፋርማሲስት ጉልህ ድርሻ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ አቶ ጫላ ዳመና በመድኃኒቶች አግባባዊአጠቃቀምና የፋርማሲሰት ኃላፊነት ገለፃ ተደርጓል፡፡
በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ ያለውን ሀገራዊ ለውጥና ለቀጣይ ስኬት የፋርማሲ ባለሙያዎች የሚኖራቸው ሙያዊና የአመራር ሰጪነት ድርሻን በተመለከተ በመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የአዳማ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰሎሞን ንጉሴ “በፋርማሲስትነቴ እኮራለሁ” በሚል መግቢያ ተነስተው ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የቅርንጫፉ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግርማ አቦ በተገኙበት በቀረቡት አጀንዳዎችና ሌሎች ሀሳቦች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ መርኃ-ግብሩ መጠናቀቁን አቶ ሰለሞን ንጉሴ ገልፀውልናል፡፡