66 የፕሌስመንት ሂማቶሎጅ ማሽኖች ስርጭት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ====================================================
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 66 የፕሌስመንት ሂማቶሎጅ ማሽኖች/Automated hematology Analyzer/ ስርጭት እየተካሄደ መሆኑን በኤጀንሲው የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ና ሪኤጀንቶች የፕሌስመንት ፕሮጀክት አስተባባሪ ጽ/ቤት ጊ/አስተባባሪ ወ/ሮ ሚዛን ገብረ ዩሀንስ ጥር 22/2012 ዓ.ም ገለጹ፡፡
በተሰራው የስርጭት ድልድል መሰረት ለአማራ ክልል 18፡ለኦሮሚያ ክልል 16፡ደቡብ ክልል 17፡ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 1፡ አፋር ክልል 2፡ሶማሌ ክልል 2፡ ድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳዳር 1፡ጋንቤላ ክልል 1፡ሀረሬ ክልል 1 በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉበሙሉ እንደሚሰራጩ ታውቋል፡፡
በዛሬው እለትም በትግራይ ከልል ለሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ 8 ሆስፒታሎች የሂማቶሎጅ 5 ሲቢሲ /ሰመረ፡ አጽብኃ፡ፊሬወይኒ፡እንትጮ እና ዳልፋጊ ሆስፒታሎች/እና 3ሲቢሲ/እንዳባጉና፡ወልቃይት እና ሰለልሃ ሆስፒታሎች/ ማሽኖቹ እንደተሰራጩ አስተባሪዋ ገልጻለች፡፡
እየተሰራጩ ያሉት ማሽኖች ከተሟላ የመመርመሪያ ግብአቶች/reagents/ጋር የሚሠራጩ በመሆናቸው ማሽኖቹ ከተተከሉ በኋላ ምንም አይነት ከግብአት ጋር የተያያዘ የአገልግሎት መቋረጥ እንደማይኖር ከወ/ሮ ሚዛን ማብራሪያ ማወቅ ተችሏል፡፡
Supply chain of compassion!!!!