ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከዋናው መ/ቤት እና ካሉት ቅርንጫፎች ከመላው ሰራተኞቹ ከወር ደሞዛቸውን በማዋጣት ለጀግናው የሀገር #መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ አልምፀሃይ ጳውሎስ እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጋሎ በተገኙበት በመከላከያ ዋና መ/ቤት ተገኝተው ለመስከረም 28/2014 ድጋፉን አስረክበዋል፡፡የጤና ሚ/ር ዲኤታ ወ/ሮ አልምፀሃይ ጳውሎስ ተጠሪ ተቋማትን በማስተባበር ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ ኤጀንሲው መከላከያ ባለበት ሁሉ መድኃኒቱንም ሆነ የህክምና ግብዓቶችን እያቀረበ እንደሚገኝ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጋሎ ሲሆኑ ይህ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ በማድረጋችን ሀላፊነታችንም ግዴታችንም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ሰራተኞችና አመራሮች የወር ደሞዛቸውን ሙሉ በሙሉ እና በግማሽ በማዋጣት ሌት ተቀን ለመከላከያ ግብዓቶች በማሰራጨት እንዲሁም የደም ልገሳ በማድረግ በአካልም በየቦታው በመገኘት ድጋፍ እንደተደረገ ተናግረው ይህም የሚበዛ ሳይሆን ያንሳል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፡፡የተደረገውን #ድጋፍ በመከላከያ በኩል የተረከቡት የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ብርጋዴል ጀኔራል አስረስ አያሌው እንደተናገሩት ቀደም ሲል የህግ ማሰከበር እንዲሁም አሁን ላይ በህልውና እና #ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ ከተጀመረ ጀምሮ መላው ህዝብና የተለያዩ ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ከእነዚህ ተቋማት በዋናነት የሚጠቀሰው የጤና ሚ/ር እንደሆነ እና ከጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የመከላከያችንን የመድኃኒት ፍላጎት በማሟላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ እንዳለ ብርጋዴል ጄነራል አስረስ ተናግረዋል፡፡ለሀገርም ሆነ ለመከላከያ ኤጀንሲው እያደረገ ያለውን የህክምና ግብዓት በማቅረብ አስተዋፅዖ ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡የኤጀንሲው ማህበረሰብ 10 ሚሊዮን ያደረጉት ድጋፍ ትልቅ ትርጉም ያለው እንደሆነና በሞራልም በግባቶችም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አክለው ገልፀዋል፡፡
አወል ሀሰን