ከአካባቢ ብክለት ነፃ በሆነ መልኩ እየሰራ እንደሆነ የጅማ ቅርንጫፍ ኢንሲሊኔተር ማዕከል አስታወቀ
የመድኃኒት አቅርቦትን በስፋት ተደራሽ እያደረገና ብክነትን በእጅጉ እየቀነሰ የመጣዉ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በተለያየ ምክንያት ጥቂት የሚባሉ መድኃኒቶች ጊዜያቸዉ ሲያልፍ ከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ የሚያስወግድበት ስርአት ያለዉ ሲሆን፤ የጅማ ቅርንጫፍ ኢንሲሊኔተርም ነዋሪዉን በማይጎዳ መልኩ እያስወገደ እንደሆነ አስታዉቋል።
ስራ ከጀመረ የአንድ ወር እድሜ ያስቆጠረዉ የጅማ ኢንሲሊኔተር ማዕከል ሀላፊ ፈዲላ ሸረፋ እንዳሉት መወገድ ጀረጃ ላይ የደረሱትን መድኃኒቶች የአካባቢን ደህንነት ባረጋገጠ መልኩ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
የኢንሲሊኔተሩ ማሽን ኦፕሬተር ኢንጂነር ሙለቤ ደመቀ በንግግራቸዉ ግብአቶቹ ከ1200 እስከ 1300 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሙቀት የማቃጠል ሂደቱን ካለፉ በኋላ የማቀዝቀዝና ብናኞቹን የሚያጣራ ሲስተም እየተተገበረ በመሆኑ ባለሞያዎችም ላይ ሆነ አካባቢዉ ላይ የጤና ጉዳት የማያስከትል እንደሆነ ገልፀዋል።
ዘጋቢ፦ አማኑኤል ወርቃየሁ
