ቅርንጫፉ በቀጥታ ስርጭት (Last mile delivery) የሚደርስባቸዉ የመንግስት ጤና ተቋማት ማሳደጉን ገለፀ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ለ274 ጤና ተቋማት የህክምና ግብዓቶችን እያቀረበ ሲሆን፤ በዚህም የጤና ፕሮግራም ግብአቶችን በቀጥታ ስርጭት (Last mile delivery) ለመንግስት ጤና ተቋማት እያደረሰ ይገኛል፡፡
ቅርንጫፉ በቀጥታ ስርጭት በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ለ94 ጤና ተቋማት ያደርስ የነበረዉን በበጀት አመቱ ወደ 154 ተቋማት ማድረስ እንደተቻለ እና ለዉጡ ከ34% ወደ 56% ማሳደጉን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ የመጋዘን አያያዝ እና ስርጭት ባለሙያ አቶ ታጠቅ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡
በተለይ በጤና ፕሮግራም ግብአቶች ቀጥታ ስርጭት የተቋማት እርካታ ተለክቶ ምላሹ ጥሩ መሆኑን ገልፀዉ፤ በበጀት አመቱ መጨረሻ የህብረተሰቡን እርካታ እንደሚለኩ ባለሙያዉ ተናግረዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የቀጥታ ስርጭት አድማሱን 62% ለማድረስ ከዋናዉ መስሪያ ቤት እና USAID Global Health Supply Chain Program Procurement and Supply Management (GHSC-PSM) ፕሮጀክት ጋር በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ አቶ ታጠቅ ተናግረዉ፤ ጤና ተቋማት የሚያቀርቡት መጠየቂያ (RRF) ጥራት ዝቅተኛ መሆን፤ የተሸከርካሪ እጥረት እና የመንገዶች አስቸጋሪ መሆን ለቀጥታ ስርጭቱ ተግዳሮት እንደሆነባቸዉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ
