በበጀት አመቱ ከሀገር ዉስጥ የመድኃኒት አምራቾች ከፍተኛ ግዥ መከናወኑ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 20 ከሚደርሱ የሀገር ዉስጥ የመድኃኒት አምራቾች ግብዓቶችን በመግዛት ያሰራጫል፤ አምራቾቹ ትልቅ የማምረት አቅም ቢኖራቸዉም ጥሬ እቃ የሚገዙበት የዉጭ ምንዛሬ አለመኖር ተግዳሮት ሆኖባቸዉ ቆይቷል፡፡
በዚህም ድጋፍ ለማድረግ በጤና ሚኒስቴር መሪነት የገንዘብ ሚኒስቴር አምራቾቹ የሚያስፈልጋቸዉን 55% የዉጭ ምንዛሬ እንዲያመቻች አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፤ በዚህ አግባብ አገልግሎቱ በበጀት አመቱ ከ 19 የሀገር ዉስጥ አምራቾች ግዥ መፈፀሙንና ከባለፈዉ አመት ጋር ሲነፃፀር 6 እጥፍ ያደገ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ገልፀዋል፡፡
አምራቾቹ በተያዘው በጀት አመት አጠቃላይ በሀገር ዉስጥ የማምረት አቅም በገንዘብ ከ8% ወደ 34% ያደገ ቢሆንም በአይነት ሲለካ 51 አይነት መድኃኒቶች ብቻ እያቀረቡ እንደሚገኙ አቶ ሰለሞን ተናግረው፤ አምራቾችን ከዚህ በላይ ለማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ ገልፀዋል ፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ
