አገልግሎቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአገልግሎቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ዙሪያ መጋቢት 29 ቀን በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ዉይይት አድርገዋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ በበኩላቸዉ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ያለበትን ደረጃ ገምግመዋል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ለምክር ቤት አባላት ተቋሙ እያከናወነ ያለዉን ሪፎርም ያስገነዘቡ ሲሆን የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርአት ERP እየፈጠረ ስላለዉ የአሰራር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ፤ የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አምራቾች 87 አይነት መድኃኒቶችን ማቅረባቸዉ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዉ የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ዉል የተገባለት የአቅርቦት ስርአት Committed Demand እና አማራጭ የአቅርቦት ምንጭ Multi-Vendor Model መተግበር እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ሌሎች የቋሚ ኮሚቴ አባላቱም ዉጤታማ የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት ሂደት ላ ፤ በሰዉ ሃይል ግንባታ ፤ የፋይናንስ ስርዓትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን በዋንኛነት የግብዓት ስርጭቱ እንዳይቆራረጥ ከክልልና ዞን ሀላፊዎች ጋር መናበብ እንደሚያስፈልግ አስታዉሰዋል።
የአገልግሎቱን G+7 የዋና መ/ቤቱን ህንፃ የምክር ቤቱ አባላት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
