በዋናው መስሪያ ቤት ለ3 ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ የተቋማዊ ግንባታ ሪፎርም ዉይይት በስኬት ተጠናቀቀ
፨፨፨፨፨፨፨፨
”ዉጤትን ማጠናከር ፤ ተግዳሮትን ማረም” በሚል መሪ ቃል የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች ከግንቦት 5_7 2017 ዓ.ም በተቋማዊ ግንባታ ሪፎርም ዙሪያ የአመራሩና ሰራተኞች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ፣ የአስተዳደርና ኦፕሬሽን ዘርፉ ቁመና ግንባታ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረዉ ዉይይት በስኬት ተጠናቋል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንዳሉት “የተቋም መገንባት ጠቀሜታዉ ትዉልድ ተሻጋሪ” መሆኑን ጠቁመዉ የስራ ባህላችን ዉጤት ተኮር እንዲሆን ሁላችንም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በትብብር መንፈስ ህብረተሰባችንን ማገልገል ይጠበቅብናል ፤ ቀልጣፋና በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነ ተቋምን በመገንባቱ ሂደት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በተጨማሪም አመራርን ማብቃት ፤ ብክነትን መቀነስ ፤ ስርቆትን ማስቀረት ፤ የተሳለጠ ስርጭት መፍጠር ፤ ዉል የተገባለት የአቅርቦት ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ፤ ERP ሲስተምን በተሟላ ደረጃ መተግበር ፤ ሴት አመራሮችን ማብቃት እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል።
የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተሮችም በሶስቱ ቀናት የተነሱ ጥቃቄዎች ላይ ሀሳባቸዉን የሰጡ ሲሆን ሰራተኞችን ለመደገፍ የአዋጁ መፅደቅ አቅም እንደሚሰጥ ፤ የኪራይ መጋዘኖችን የማሻሻልና የማጠፍ ስራ እንደሚሰራ ፤ የ2016 ዓ.ም እና 2017 ዓ.ም ያልተወራረዱ ሂሳቦችን በመናበብና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ መዝጋት እንደሚገባ ፤ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ስልጠናዎችን ወደ ዉጤት መቀየር እንደሚያስፈልግ ፤ ብክነትን አሁን ከደረስንበት መሻሻል በላቀ ደረጃ መቀነስ አለብን ፤ የግዥ ሂደትን ማሳጠር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።
በዋናዉ መስሪያ ቤት የዉይይት መድረክ አገልግሎቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ እና ዘመናዊ አሰራርን (Digitization) በመከተል የፈጠራ ስራዎችን ያከለ ትጉ የለዉጥ አመራርና ሰራተኞች ሊኖረዉ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
#ማገልገል ክብር ነዉ
