በዘላቂነት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ሰጪነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የመድኃኒትና የህክምና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ክትትል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበበ በየነ እንዳሉት ተቋሙ የጀመረዉን የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎችን በእቅድና በስታንዳርድ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዉ አመራሮችና ባለሞያዎች እያሳዩ ያለዉን ትጋት በማመስገን በዘላቂነት ጥራት ያለዉ ስራን ለመስራት ክትትልና ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የግሎባል ካይዘን ተቋም ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደረጄ ቶሎሳ በንግግራቸዉ አገልግሎቱ ደንበኞቹን በላቀ ደረጃ ለማገልገል ደረጃዉን የጠበቀ (Standardized) በማድረግ ሂደት ዉስጥ የአመራሩና የባለሞያዎች ዝግጁነት መልካም እንደሆነና ለክህሎት ሽግግርም እየተካሄዱ ያሉ ጥረቶች አበረታች እንደሆኑ ተናግረዋል።
በተያያዘም ብክነትን መቀነስ ፤ የግዥ ሂደትን ማሳጠር ፤ የፋይናንስ አፈፃፀምን ማጎልበት ፤ የተሽከርካሪ አጠቃቀምና አያያዝን ማጠናከር እንዲሁም የሰዉ ሃይል አቅም ግንባታ ዙሪያ የካይዘን ተቋም ከአገልግሎቱ ጋር ዉጤታማ ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ አስተባባሪዉ አስረድተዋል።
የአገልግሎቱ አመራሮችና ቡድን መሪዎችም ስራዎችን በጥራት በላቀ ደረጃ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን Standard Operating Procedure (SOP) አይተኬ እንደሆነ ገልፀዋል።
የአገልግሎቱ ቡድን መሪዎች በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት SOP ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ዶክመንት በማዘጋጀት ዉጤታማ ስራን እንደሚሰሩ ይጠበቃል።
#ማገልገል ክብር ነዉ
