• Call 8772

  • Please specify the group

ለኤጀንሲው በህግ የተሰጠው ሀላፊነት

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በጤና ጥበቃ ስር በአዋጅ ቁጥር 553/1999 የተቋቋመ መንግሥታዊ ድርጅት ነው፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 9 የኤጀንሲውን ተግባርና ኃላፊነቶች በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ አንቀጹ እንደሚገልፀውም ኤጀንሲው የሚከተሉትን ሥልጣንና ተግባራት ያከናውናል፡፡

  1. በመድኃኒት ፈንድ በመጠቀም በሀገሪቱ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ላይ ያተኮሩ ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድኃኒቶችን በበቂ መጠን፣ በተመጣጣኝ ዋጋና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመንግሥታዊ የጤና አገልግሎት ተቋማት ማቅረብ የሚያስችል ቀልጣፋና ብቃት ያለው የግዥና የስርጭት ስርዓት ይዘረጋል፣ ይተገብራል፤
  2. ዘመናዊ የክምችት አስተዳደር ለማስፈን የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ተመጣጣኝና ተገቢ የመድኃኒት ክምችትና ያልተቋረጠ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል፤
  3. የክምችትና የስርጭት አውታሮችን ፍትኃዊና ውጤታማ በሆነ መልኩ ያስፋፋል፣ ያጠናክራል፤
  4. አግባብ ባለው አካል ደህንነታቸው፣ ፈዋሽነታቸውና ጥራታቸው የተረጋገጠ መድኃኒቶችን ለመንግሥት የጤና ተቋማት ያቀርባል፣ አግባብ ሆኖ ሲገኝ በበቂ መጠን ሊቀርቡ ያልቻሉ የተመረጡ መድኃኒቶችን ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት መንግሥታዊ ላልሆነና ለግል የጤና ተቋማት ያቀርባል፤
  5. የማጓጓዣ ሥርዓትን በማመቻቸት መድኃኒቶችን በቀጥታ ለወረዳዎች ሆስፒታሎችና እንደ አመቺነቱ ለጤና ጣቢያዎች ያድርሳል፤
  6. በዘርፉ ከሚዘረጋው ስርዓት ጋር የሚጣጣም ዘመናዊ የሎጂስቲክ መረጃ ልውውጥ ስርዓት ይዘረጋል፤
  7. የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የግዥ፣ የስርጭት፣ የማከማቸትና የማጓጓዝ እቅድ በማዘጋጀት ይተገብራል፣ አፈፃፀሙንም ይገመግማል፤
  8. በሚያከናውናቸው የሙያ ዘርፎች ላይ ሙያዊ የምክር አገልግሎትና ሥልጠና ይሰጣል፤
  9. አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አማካሪ ኮሚቴዎችን ያቋቁማል፣ ሥራቸውን ይመራል፣ ያስተባብራል፤
  10. ለሚሰጠው አገልግሎት ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ክፍያ ያስከፍላል፤
  11. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
  12. ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፡፡

Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service – EPSS

X