የአልትራ ሳውንድ እና የዲጅታል ኤክስሬ ማሽኖች ማሰራጨት ተጀመረ

300 የአልትራ ሳውንድ እና 50 የዲጅታል ኤክስሬ ማሽኖች ማሰራጨት መጀመሩን በኤጀንሲው ከፍተኛ የክምችት አስተዳደር ኦፊሰር አቶ እንዳልካቸው መኮንን ተናገሩ፡፡
አልትራ ሳውንድ ማሽኖቹ ለአዲስ አባባ 15፣ አማራ 75፣ ኦሮሚያ 47፣ ትግራይ 49፣ ደቡብ 53፣ ሐረሪ 1፣ ጋምቤላ 5፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 6፣ አፋር 13 ክልሎች ሥር ለሚገኙ የጤና ተቋማት እየተላከ መሆኑን አቶ እንዳልካቸው ጠቁመዋል፡፡
ስርጭቱ ከሰኔ 20 ቀን ጀምሮ መሰራጨት የተጀመረ መሆኑን ኦፊሰሩ ተናግረው አዲስ አበባና ትግራይ ክልል ጤና ጣቢያዎች በጤና ሚኒስቴር በተላከው የስርጭት መርሃግብር መሠረት ማሽኖቹ መላካቸውን አቶ እንዳልካቸው አስታውቀዋል፡፡
የዲጅታል ኤክስሬ ማሽኖች ደግሞ ለትግራይ 4፣ አፋር 2፣ አማራ 13፣ ኦሮሚያ 16፣ ሶማሌ 2፣ ጋምቤላ 1፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 2 እና ደቡብ ክልል 10 ይወስዳሉ ተብሏል፡፡
በቅርቡ የዲጅታል ኤክስሬ ማሽኖችን በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ሰንዳፋ እና መልከ ጡሪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መላኩን አቶ እንዳልካቸው ተናግረው ስርጭቱን ለማካሔድ የተቋማት የዝግጅት ዳሰሳ በባለሙያዎች እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡
ማሽኖቹን ለመግዛት አጠቃላይ 208.05 ሚሊየን ብር የፈጀ መሆኑን ኦፊሰሩ አስታውቀው ግዢው ከዘላቂ ልማት ፈንድ በጀት በጤና ሚኒስቴር ጥያቄ የተገዛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ለአልትራ
ሳውንድ 15.6 ሚሊየን ብር እንዲሁም ለዲጅታል ኤክስሬ ማሽኖች 192.7 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን አቶ እንዳልካቸው
አስታውቀዋል፡፡
የአልትራ ሳውንድና የዲጂታል ማሽኖች የጤና ችግርን ለመለየት እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋሉ ሲሉ ኦፊሰሩ ከዝግጅት ክፍሉ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል፡፡ )�^G7�