በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር እና ልዑካናቸው ከኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡ ====================================================
በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር የሆኑት ሚስተር ቶርበጀን ፒተርሰን /Torbjorn Petterson/ እና ልዑካናቸው ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዛሬ መስከረም 21/2012 ዓ.ም በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ስለ ኤጀንሲው አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና አሰራር በዋና ዳይሬክተሩ በዶ/ር ሎኮ አብርሃም እና በም/ዋ/ዳይሬክተሯ ዶ/ር ቃልኪዳን ላቀው በኩል ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ ሚስተር ፐተርሰን በተደረገላቸው ሰፊ ገለጻ ግንዘቤ እንዳገኙ ጠቁመው በሚቀጥለው ህዳር ወር ብዙ የስዊድን ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ እና በመድሃኒት አቅርቦት በኩል ባሉ መልካም የገበያ አማረጮች ኩባንያዎች የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ የራሣቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት እንዲሁም ስለ ኤጀንሲው ሁኔታ ኩባንያዎች ግንዛቤያቸው ከፍ እንዲል የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩ አምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡ Supply chain of compassion!!!