የእናቶች የሕይወት አድን ጤና ግብዓቶች ወደ ተቀናጀ የመድኃኒት አስተዳደር ስርዓት /IPLS/ ተቀላቀሉ፡፡

October 21, 2019ፊውቸርድ ዜና
በአለም የጤና ድርጅት የተመረጡ 7 የእናቶች የሕይወት አድን ጤና ግብዓቶችን ወደ ተቀናጀ የመድኃኒት አስተዳደር ስርዓት /IPLS/ መቀላቀላቸውን የእናቶችና ሕፃና ግዥ ትንበያ ባለሙያ አቶ ኃይለኢየሱስ ወሠን አስታወቁ፡፡
መድኃኒቶቹ 1. Magnesium sulphate 2. Oxytocin 3. Ergometrine 4. Calcium gluconate 5. Mifepristone + Misoprostol 6. Misoprostol 200 mcg 7. Misoprostol 25 mcg ናቸው ብለዋል።
እንደ ባለሙያው ገለፃ IPLS ኤጀንሲው እና የጤና ተቋማት የሚጠቀሙበት የመድኃኒት አስተዳደር ስርዓት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
IPLS የጤና ተቋማት ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የመድኃኒት ስርጭት እንዲኖር እንደሚያስችል ገልፀው ብክነትን እንደሚቀንስና የመድኃኒቶቹን እጥረት እንደሚያስወግድ አብራርተዋል፡፡
IPLS ኤጀንሲው ከተቋቋመበት ጊዜ አስንቶ የሚጠቀምበት ስርዓት መሆኑን አቶ ኃይለኢየሱስ አክለዋል፡፡