ኤጀንሲው የሥራ ሂደቶችን አሠራር በመፈተሽ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

January 17, 2020ፊውቸርድ ዜና
የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት (QMS) በመተግበር ISO 9001: 2015 ሰርተፊኬት ለማግኘት እየሠራ ነው፡፡
በዚህም ትግበራ የውስጥ አሠራሮችን በጥራት አስተዳደር ሥርዓት የውስጥ ኦዲት ቼክ ሊስት (QMS Internal audit Check list) በመጠቀም መፈተሽ እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ሥራዎች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲካሄዱ ማድረግ ዋነኛ መስፈርቱ ነው፡፡
ይህንንም የውስጥ ኦዲት የሚያከናውኑ ባለሙያዎች በማሰልጠን በዋናው መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙ የሥራ ሂደቶችን የመፈተሽ ሥራ ጀምሯል፡፡