ከሎጅስቲክ አገልግሎት ሠጪና ሌሎች የኤጀንሲው ባለድርሻዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
December 30, 2020Uncategorized @am
ኤጀንሲው ከሎጅስቲክ አገልግሎት ሠጪ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ከታህሣሥ 03 እና 04 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄደ።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በመክፈቻ ንግግራቸው መድረኩ ከኤጀንሲው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ያሉትን ማነቆዎች በመለየት ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሆነና የመድኃኒት ግዥ ጊዜን በመቀነስ አቅርቦቱን ከፍ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።መድኋኒትን ለማቅረብ የሎጅስቲክ ችግር እንደሚያጋጥም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዉ ባለድርሻ ተቋማቱ ከተቋቋሙበት ግብ ባሻገር ለህብረተሠቡን መድኃኒትን ተደራሽ ለማድረግ ኤጀንሲውን ሊደግፉና ትኩረት ሊሠጡት እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።በቀጣይ የጋራ ችግሮቻቸውን በመፍታት ለማህበረሠቡ መድኃኒት ተደራሽ ለማድረግ በኤጀንሲውም በባለድርሻ አካላቱ ያሉ የአሠራር ማነቆዎች ተለይተዋል።በምክክር መድረኩ 13 ተቋማት እንዲሣተፉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኋኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ፣ ኢንሹራንስ፣ ባንኮች፣ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ሌሎችም ተሣትፈዋል።ባለድርሻ አካላቱ ኤጀንሲው መድኃኒት የሚያጓጉዝበት የሞጆ ደረቅ ወደብን ጎብኝተዋል።
በፀሎት የማነ
