ኤጀንሲው ለትግራይ ክልል የተለያዩ ግብዓቶችን እያሰራጨ እንደሆነ ተገለጸ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለትግራይ ክልል የተለያዩ ግብዓቶችን እያሰራጨ መሆኑን የስርጭት ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን አብሬ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አስታወቁ፡፡ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር ዘመቻ ከተካሄደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ግብዓቶችን ያሰራጨ ሲሆን አሁንም የግብዓቶች ስርጭትም ቀጣይነት እንዳለው ባለሞያው ገልጸዋል፡፡የተሰራጩት ግብዓቶችም Chemicals and Reagents, Pharmaceuticals, Medical Supplies እና Medical Equipments ሲሆኑ በአጠቃላይ 151 ሚሊዮን 318 ሺህ 157.92 ብር ወጪ የተደረገባቸው ግብዓቶች መሰራጨታቸው ተገልጿል።ስርጭቱም ለ71 ጤና ተቋማት መከናወኑን አቶ ተስፋሁን አክለዋል።ሂሩት ኃይሉ