ኤጀንሲው የኮቪድ 19 የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የኮቪድ 19 የክትባት መድኃኒቶችን ለሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እየተሠራጨ መሆኑን የስርጭት ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን አብሬ አስታወቁ።የክትባት መድኃኒት ስርጭቱ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው የስርጭት ቁጥር መሠረት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ለኦሮምያ ፣ለአማራ ፣ ለደቡብ ብሔር ብሔረሠቦችና ሕዝቦች ፣ ለሲዳማ ፣ ለጋምቤላ፣ ለትግራይ፣ ለአፋር፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ለሶማሌ፣ ለሀረሪና ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እንደተሰራጨ ተገልጿል፡፡በስርጭቱ ወቅት ቅዝቃዜው በትክክል መጠበቁን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ በሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ መገጠሙንና ይህም ክትባቱ ጥራቱ እንደተጠበቀ ለጤና ተቋማት መድረሱን ለማረጋገጥ እንደሚረዳል አክለው ገልፀዋል።ኤጀንሲው 2 ሚሊየን 184ሺህ ዶዝ የክትባት መድኃኒት የተረከበ ሲሆን 104 ሚሊየን 96ሺህ 70 ሚሊየን ብር የገንዘብ ወጪ እንዳላቸው ቡድን መሪው ተናግረዋል፡፡በተያያዘ ዜና ለክትባት አገልግሎቱ የሚውል አልኮል እና ሲሪንጅ የተሠራጨ ሲሆን 1 ሚሊየን 473 ሺህ 519 የብር መጠን እንዳላቸው በቃለ መጠይቁ ተብራርቷል፡፡
በፀሎት የማነ