የድሬደዋ ጤና ቢሮ ከኤጀንሲው ቅርጫፍ ጋር ተደጋግፎ እየሠራ እንዳለ ተገለፀ

ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ድሬደዋ ቅርጫፍ ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፈጠር የጤና ግብአቶችን ያሉትን መድሀኒቶች ለህብረተሠቡ በማድረሥ ተደጋግፈው እየሠሩ መሆናቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፁ።ያሉብንን የጋራ ችግሮች ለመፈታት የጤና ቢሮው አና የቅርጫፉ ሀላፊዎች ያሉበት የጋራ ቡድን ተቋቁሞ የአቅርቦት ችግሮች በየ ጊዜው እየገተገመገሙ የጋራ መፈትሄ እንሰጣለን ብለዋል።በኮረና ተፅእኖ እንደሀገር በመድሀኒት እጥረቶች ያስከተለውን ጫና እንገነዘባለን ያሉት ሀላፊዋ ቅርጫፉ ግን ያለውን ግብአቶች ይሰጠናል ብለዋል።
አንዳንድ ጊዜ የህክምና ግብአቶች ከመአከል ተልከው በተለያየ ምክንያት የሚዘገዩበት ሁኔት እንደነበር አስታውሰው ይህ የጋራ ቡድን ከኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች በአካል መጥተው እንድዋቀር ከተደረገ በሗላ ግን ግብአቶቹ በፍጥነት ይደርሳሉ ብለዋል።በፖሊዮ ክትባት እጥረት አጋጥሞ በጊዜው እንደነበር አስታውሰው ከላይኛው አካል ጋር በመነጋገር ወዳውኑ እነደተፈታ አስረድተዋል።የወባ አጎበሮች ስርጭትን ጨምሮ የ ሌሎቾ የህክምና ግብአቶችን ቅርጫፍ በቀጥታ እስከ ወረዳወች በየጊዜው እንደሚያደርስ እና ቢሮው ከዚያ በኋላ ወደ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ባለው የጤና አደረጃጀት በኩል ይሠራጫል ብለዋል።በሆስታሎችም ሆነ በጤና ተቋማት ወርሀዊም ሆነ አመታዊ የመድሀኒት የፍጆታ መጠን በወቅቱ እና በትክክል ያለመመጠን እጥረቶች አንዳሉ ሀላፊዋ ተናግረው ይህሞ በኤጀንሲው የግብአት አቅርቦት ላይ ጫና እንዳለው እንረዳለን ብለዋል።ኤጀንሲው እንዴ ሀገር ትልልቅ የህክምና ግብቶችን ግዥ የሚያከናውን በመሆኑ እና በማሠራጨቱ ሊደነቅ የሚገባው ነው ወ/ሮ ለምለም የተናገሩት።ቅርጫፉ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በድሬዳዋ ፣ሀረሪ ፣ኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች ለሚገኙ ከ 9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህዝቦች ለ68 ወረዳወች ለ247 የመንግስት ጤና ጣቢያወች ፣ 19 የመንግስት ሆስፒታሎች እንድሁም ለመከከላከያ አና የፌደራል ፖሊስ ሆስፒታሎችን ጨምሮ ለግል የጤና ተቋማትም ጭምር በቀጥታ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን የድሬዳዋ ቅርጫፍ ሰራ አስኪያጅ አና የምስራቅ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት አስናቀች ለችሳ ተናግረዋል።ከድሬደዋ፣ ከሀረሪ ፣ኦሮሚያ ፣ሱማሌ ክልል የጤና ቢሮወች ጋር በመቀናጀት በትብብር መደበኛ አና የጤና ፕሮግራም መድሀኒቶችን በየ ጊዜው አንደሚያሰራጩ አስረድተዋል።
አወል ሀሰን