ቦርዱ የኤጀንሲውን የ9 ወር አፈፃፀም ገምግሞ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ቦርድ አባላት የኤጀንሲውን የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ክንውን ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በመገምገም አቅጣጫዎችን አስቀመጠ፡፡ ኤጀንሲው በ9 ወራት ውስጥ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ለቦርድ አባላቱ ያቀረበ ሲሆን በፕሌስመንት ግዥ የፈፀማቸውን ሪኤጀንቶች በጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ባለመወሰዳቸው በኤጀንሲው ላይ ያደረሠውን ኪሣራ ኤጀንሲው ባዘጋጀው ጥናት ለአባላቱ ቀርቧል፡፡ 11 ቢሊዮን በላይ ዋጋ የነበራቸውን የህክምና ግብአቶችን እንድሁም የ371 ሚሊዮን ብር መድሃኒት ለትግራይ ክልል በማሰራጨት የህይወት አድን እና መሠረታዊ መድኃኒቶችን ለህብረተሰቡ ኤጀንሲው ማድረስ መቻሉ በጥንካሬ ተገምግሟል፡፡
ባለፈው ሩብ አመት ቦርዱ ተጠንተው እንዲቀርቡለት በሰጠው ግብረመልስ የፕሌስመንት በአቅራቢዎች ማሽኖች በነፃ ተሰጥተው የመርመሪያ ሪኤጀንቶች 70% ኤጀንሲው ከውጭ ገዝቶ በጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ባለመወሰዳቸው ያጋጠሙት ችግሮች የተጠና ጥናት ቀርቧል፡፡ CBC እና chemistry ማሽኖች መቅረባቸው በአንድ ናሙና እስከ 47 አይነት ምርመራዎችን ማድረግ ያስቻለ እንደነበረ ተገልጻል ፡፡ ሆኖም ግን ቅንጅት አለመኖር ፡የእውቀት ክፍት እንዲሁም የላቦራቶሪ ክፍያ ማነስ በዘርፉ የታዩ ክፍተቶች እንደነበሩ ተብራርቷል፡፡ የአገር ውስጥ የመድኃኒት አቅራቢዎች የመድኃኒት አቅርቦት አፈፃፀም ማነስ በአገሪቱ የተቆራረጠ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲኖር ማድረጉንና በአቅራቢዎቹ በኩልም የነበሩ ተግዳሮቶችና ችግሮቻቸውን ቀርበዋል፡፡ አቅራቢዎቹ ለገቡት የውል ስምምነት ተገዥ መሆን እንዳለባቸው እና ባቀረቡት ልክ ክፍያ መፈጸም እንደሚገባ የተገመገመ ሲሆን በሌላ በኩል በመካከላቸው የምርት ድግግሞሽን አስወግደው የሚጠቀሙባቸው የማሸጊያ ማቴሪያሎች ልክ የምርቱ አካል ተደርጎ ከቀረጥ ነጻ እድገባላቸው ቢደረግ አፈጻጸማቸው እንደሚጨምር በጥናቱ ተመላክቷል ፡ ምክረ ሀሳቦቹም በሶስት በመክፈል በመንግስት፡በአገር ውስጥ አቅራቢዎች በራሳቸው እንድሁም በአምራቾቹ ከመንግስት ጋር በመሆን የሚፈቱ ጉዳዮች ተለይተዋል ፡፡
አጀንሲው በበጀት አመቱ 109 አይነት መድሃኒቶችን በ890 ሚሊዮን ብር ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች ገዝቶ ለጤና ተቋማት ለማቅረብ ውል ቢኖረውም እስካሁን ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች መቅረብ የቻለው 25 አይነት መድሃኒቶች በ140 ሚሊዮን ብር ይህም አፈጻጸሙ 23% እንደነበር ተገምግሟል፡፡ ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ ያለባቸው ሆሰፒታሎች መኖራቸው በኤጀንሲው የመድሃኒት አቅርቦት ላይ ጫናው ከፍተኛ በመሆኑ በዱቤ ላይ ዱቤ እንዳይስተናገዱ እና ቀሪውም ብር ከጤና ሚንስቴር ጋር በመነጋገር መሰብሰብ እንዳለበት ተገልጻል፡፡
የዋና መ/ቤቱ ህንፃ ግንባታ በአስቸኳይ ለማስጀመር ከግል ድርጅት ጋር የነበረውን ውል ባለሃብቱ ማከናወን ስላልቻለ ወደ መንግስታዊ ተቋም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ማስተላለፍ ቢሞከርም ህንጻውን ለመጨረስ ከፍተኛ ክፍያ ኤጀንሲው እንደተጠየቀ ተገልጻል፡፡ግልጽ ጨረታ ወጥቶ ሌሎች አማራጮች እንዲተገበሩ በማለት ቦርዱ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ቦርዱም ሪፖርቱን ተመልክቶ የሪፖርቱን አቀራረብ በማድነቅ የኤጀንሲው ሰራተኞችና አመራሮች በጋራ ያሳዩት አፈፃጸምን የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ይናገር ደሴ አድንቀው በተለይም የህይወት አድን፣ መሠረታዊ መድኃኒቶች፣ የወባ፣ ኤች. አይ. ቪ መድኃኒቶችና የጤና ፕሮግራም ግብዐቶች ስርጭትን አበረታተዋል፡፡
በመጨረሻም ከሞጆ ደረቅ ወደብና ከአየር መንገድ ግብዐቶች በፍጥነት ማንሳት መቻሉ፣ ለግዥ የሚወስደውን ጊዜ ለማሳጠር ከደንበኛ እርካታ ጋር የተሰሩ ተግባራትን፣ ከጤና ሚኒስቴርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀው ቀጣይነት እንዲኖረው አሣስበዋል፡፡
አወል ሀሰን