የሐዋሳ ቅርንጫፍ ካለፈው ዓመት ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ የካይዘን ፍልስፍናን በአግባቡ በመተግበሩ 65 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሰ ገለጹ፡፡ ገቢው ሊገኝ የቻለው ጥቅም ላይ ሳይውሉ በመጋዘን ተከማችተው የነበሩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በመለየት ለጤና ተቋማት በማሰራጨቱ፣ ራክ ለነጌሌ ቦረና ቅርንጫፍ እንዲሁም ፓሌት ራኮችን ለአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ በማሰራጨቱ የተገኘ ውጤት እንደሆነ አቶ […]