በሐዋሳ ከተማ የተገነባው ዘመናዊ የመድኃኒት ማስወገጃ ኢንሲኔሬተር የሙከራ ሥራ መሥራት እንደ ጀመረ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሠ ዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2011ዓ.ም. በፌስ ቡክ ገጻቸው አስነበቡ፡፡ ቀደም ሲል ግንባታው ተጀምሮ የነበረው የሐዋሳው ቅርንጫፍ ዘመናዊ የመድኃኒት ማስወገጃ ኢንሲኒሬተር በታቀደለት የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባታውና የማሽነሪዎች ተከላ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ከሚያዝያ 22/2011 ጀምሮ የሙከራ ስራ ጀምሯል ብለዋል፡፡ […]