የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባለፉት 9 ወራት ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያላቸው የቤተሠብ ምጣኔ እንዲሁም የእናቶችና ሕፃናት ግብዓቶችን እንዳሠራጨ የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ባለሙያ አቶ አድማሱ ውብአንተ ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለጹ፡፡ ኤጀንሲው ግብዓቶቹን ባሉት 18 ቅርንጫፎች አማካኝነት በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ የጤና ተቋማት ያሠራጨ ሲሆን ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 1 ቢሊዮን 134 ሚሊየን […]