በግዢ ሂደት ላይ የነበሩ ለHIV Viral Load ምርመራ የሚውሉ ከ50 በላይ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችና ግብዓቶች ወደ ኤጀንሲው መጋዘን መግባታቸውን የፕሮግራም ላብራቶሪ ግብዓቶች ትንበያና ገበያ ጥናት ባለሙያ አቶ ሳሙኤል ወንድወሰን ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ለዝግጅት ክፍሉ አስታወቁ፡፡ ሪኤጀንቶቹ እና ግብዓቶቹ በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት ለተመረጡ 19 የHIV Viral Load ምርመራ ማእከሎች እንደሚሰራጩና ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚደረጉ ባለሙያው አብራርተዋል፡፡ […]
ኤጀንሲው ለስኳር በሽታ የሚውሉ Insulin Isophane Human100.Iu/ml in 10 ml injection ማስገባቱን የመደበኛ መድኃኒት ግዥ ባለሞያ ወ/ሮ ሜቲ ገመቹ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡ ወ/ሮ ሜቲ መድኃኒቶቹ (61) ፓሌት እንደሆኑና በህዳር ወር መግቢያ ላይ በዋናው መ/ቤት Main 3 እና አዲስ አበባ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ መጋዘን መግባታቸውን ባለሞያዋ ገልጸዋል፡፡ መድኃኒቶቹ ከ325 ሺህ የአሜሪካ ዶላር […]
ኤጀንሲው በሀገሪቱ በመጭው ጊዚያቶች ሊከሰቱ የሚችሉ ለወባ ወረርሽኝ የሚውሉ አርቲመትር + ሉሚፋንትሪን (20+120) ሚ.ግ (ኳርተም) መድኃኒቶችን እያሠራጨ እንደሆነ የክምችት አስተዳደር ባለሙያ አቶ በረከት ተዘራ ዛሬ ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡ ኤጀንሲው ከሕብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት በተላከለት መረጃ መሠረት ለ304 ሺህ 200 ሰዎች የሚውል መድኃኒት እያሠራጨ እንደሚገኝና ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንዳላቸው ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ ወረርሽኙን […]
ኤጀንሲው በሐረር ከተማ ለተከሠተው የኩፍኝ ወረርሽኝ የሚዝልስ /ኩፍኝ/ ክትባት መድኃኒት ማሠራጨቱን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ለዝግጅት ክፍሉ አስታወቁ፡፡ ወረርሽኙ በተከሠተባቸው ወረዳዎች የሚገኙ ከ5 ዓመት በታች ላሉ 15 ሺህ 298 ሕፃናት የሚውል የክትባት መድኃኒት ለማሠራጨት ኤጀንሲው ዝግጅቱን አጠናቋል ሲሉ ባለሙያዋ አብራርተዋል፡፡ ወረርሽኙ በ3 ወረዳዎች ላይ መከሠቱንና ወረዳዎቹም ሶፊ፣ ይረር እና ድሬ ታየር […]
ኤጀንሲው በ3 ቅርንጫፎች ስር ለሚገኙ የተመረጡ 251 ጤና ጣቢያዎች የቀጥታ የመደበኛ መድኃኒት ስርጭት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የመደበኛ መድኃኒቶች የክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ት ስምረት የማነ ዛሬ ህዳር 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለፁ፡፡ ባለሙያዋ ኤጀንሲው ከጤና ሚኒስቴር ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቀው ስርጭት የሚካሄድባቸው ቅርንጫፎችም ባህርዳር፣ ደሴ እና ጎንደር ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ወ/ት ስምረት በባህርዳር ቅርንጫፍ 374 […]
ከስዊዲን የመጡ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲን ጎበኙ፡፡ የልዑካን ቡድኑ በስዊዲን የጤና ሚኒስቴሯ ሊና ሃሌንግሬ የሚመራ ሲሆን የስዊዲን የመንግስት ኃላፊዎች እና አለም አቀፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ተገኝተው ኤጀንሲውን ጎብኝተዋል፡፡ ስዊዲን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን አንስቶ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት እንዳላትና አሁንም የጤና ሴክተሩን ግንኙነትና ኢንቨስትመንቱን ለማጠናከር መምጣታቸውን በስዊዲን ኤምባሲ አስተባባሪ አቶ […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከሕዳር 12–15/2012 ዓ.ም. ለሚካሄደው የፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ መሆኑን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለጹ፡፡ የፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ በአገር አቀፍ ደረጃ በሕዳር ወር አጋማሽ እንደሚካሄድ ባለሞያዋ ገልፀው የክትባት መድኃኒቶቹን በኤጀንሲው 15 ቅርንጫፎች አማካኝነት እያካሄደ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ባለሙያዋ ክትባቱ […]
ኤጀንሲው ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. “ደም ለግሠን ሕይወት እናድን” ለተሠኘው የደም ልገሣ ዘመቻ ከ121 ሺህ በላይ ባለ 350 ሚ.ሊትር የደም መሠብሠብያ ከረጢት ስርጭት ማካሄዱን የክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ገለፁ፡፡ ባለሙያዋ የደም መሠብሠብያ ከረጢቶቹ ከ600 ሺህ ብር በላይ ዋጋ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ ኤጀንሲው በአሁኑ ሠዓት የተሠበሠበውን ደም ከኤች.አይ.ቪ፣ ጉበት እና ጨብጥ በሽታዎች ለመመርመር የሚውል […]
ኤጀንሲው ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያላቸው የፖሊዮ ክትባት መድኃኒቶችን በበጀት ዓመቱ ስርጭት ማካሄዱን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ገለጹ፡፡ የፖሊዮ በሽታ ፖሊዮ በተባለ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ እንደሆነና ጭንቅላት እና ህብረሠረሠርን በማጥቃት የሠውነት አካልን ፖራላይዝ /ሽባ/ ያደርጋል ሲሉ ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡ የፖሊዮ በሽታን ለመከላከል ሕፃናትን ወቅቱን በጠበቀ መልኩ የፖሊዮ ክትባት ማስከተብ እንደሚገባና […]