ከስዊዲን የመጡ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲን ጎበኙ፡፡ የልዑካን ቡድኑ በስዊዲን የጤና ሚኒስቴሯ ሊና ሃሌንግሬ የሚመራ ሲሆን የስዊዲን የመንግስት ኃላፊዎች እና አለም አቀፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ተገኝተው ኤጀንሲውን ጎብኝተዋል፡፡ ስዊዲን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን አንስቶ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት እንዳላትና አሁንም የጤና ሴክተሩን ግንኙነትና ኢንቨስትመንቱን ለማጠናከር መምጣታቸውን በስዊዲን ኤምባሲ አስተባባሪ አቶ […]