የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ በድጅታል ቴክኖሎጂ የታቀፈ የተቀናጀ የአሰራር ስርዓትን ስራ ላይ ማዋል ተገቢ መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድሃኒት አቅርቦት ስርዓቱን ድጅታላይዝ በማድረግ በቅርቡ ስራ ላይ በሚያውለው የተቀናጀ የመረጃ ስርአት (Enterprise Resource Planning ERP )ትግበራ ሂደት አስመልክቶ ከፓርራማ አባላት ጋር ሚያዚያ […]