Category description for “News”
የህክምና ግብአቶችን የመጨረሻው ጠቃሚ ጋር ለማድረስ የሚውሉ በመንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የተገዙ 62 ተሽከርካሪዎች የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የለጋሽና አጋር ድርጅት ተወካዬች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለአገልግሎቱ 19 ቅርንጫፎች የርክክብ ስነስርአት በሚሊኒየም አዳራሽ ተከናውኗል። የቀጥታ ስርጭት ተደራሽነት ለማስፋፋት አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችን በማስተባበር ከጋቪ ፣ ከአፍሪካ […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ከአጋር አካል ድርጅቱ Clinton Health Access lnitiative(CHAI) ልዑካን ቡድን ጋር ድጋፍ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል። በዉይይቱ የአገልግሎቱ አሁናዊ የአቅርቦት ሰንሰለት ምን እንደሚመስል ፣ እየተተገበሩ ያሉ የዲጂታል አሰራሮች እንዲሁም ስትራቴጅክ እቅድ ዶ/ር አብዱልቃድር በዝርዝር አቅርበው ፤ በተለይም የክትባቶች ቀጥታ ስርጭትን ለማሳደግ ፣ የቀዝቃዛ ሰንሰለት መጋዘኖች […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በቅርብ ቀን ስራ ላይ የሚያውለው እጅግ ዘመናዊ የተቀናጀ “ERP_SAP” የተባለውን ፕሮጀክት አሁን ያለበት ደረጃ ምን እንደሚመስል የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ሰራተኞች እና የፕሮጀክቱ ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አማካሪ ወ/ሮ ሰሚራ ሱልጣን እና የዲጅታል ሄልዝ ባለሙያወች በተገኙበት ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል። የመረጃ ስርዓቱ እንደ ሀገር የተያዘውን የጤና ስርአት […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የERP ቴክኖሎጂ አካል የሆነውን SAP ለመተግበር አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናበው የ2016 ለቆጠራ የERP ቴክኖሎጂ SAP መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልሎት ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸው ገለፁ። ቆጠራውን ለሚያስተባብሩ እና ለሚቆጥሩ ሙያተኞች የቅድመ ቆጠራ ኦሬንቴሽን ሰሞኑን ተሠጥቷል። የህክምና ግብአቶች አመታዊ ቆጠራ ሲደረግ በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት እና በጥንቃቄ መሆን […]
የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ በድጅታል ቴክኖሎጂ የታቀፈ የተቀናጀ የአሰራር ስርዓትን ስራ ላይ ማዋል ተገቢ መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድሃኒት አቅርቦት ስርዓቱን ድጅታላይዝ በማድረግ በቅርቡ ስራ ላይ በሚያውለው የተቀናጀ የመረጃ ስርአት (Enterprise Resource Planning ERP )ትግበራ ሂደት አስመልክቶ ከፓርራማ አባላት ጋር ሚያዚያ […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በተለያዩ ሞጅሎች ላይ ለሰራተኞች ሲሰጥ የነበረዉን ስልጠና ለማጠናቀቅ የመጨረሻዉን ዙር ስልጠና በአዳማ እና በሀዋሳ ከተማ እየሰጠ እንደሚገኝ የኢ.አር.ፒ ፕሮጀክት የለውጥ ስራ አመራር ባለሙያ ወ/ሮ አድና በሬ ተናግረዋል፡፡ P2P ፣ In2Rep ፣ H2R ፣ EHS ፣ S2S ፣ I2R ሞጅሎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉን ስልጠና ባለፉት ሳምንታት ማጠናቀቁን እና EWM ፣ TM ፣ […]
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ትላንት ማምሻዉን ባቡል ኸይር ድርጅት ዉስጥ ለሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች እና ለተቸገሩ ወገኖች የኢፍጣር መርሀ ግብር ያካሄደ ሲሆን ፤ በመርሀ-ግብሩ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ፤ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ፤ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም የባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ሀናን ሙሀመድ ታድመዋል፡፡ የመርሀ-ግብሩ ዋና አላማ ከማህበረሰባችን ጋር […]
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከመጋቢት 2/2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሞጅሎች ላይ የሲስተም ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል ፤ በዚህም P2P 3ተኛ ዙር F2R ፣ EWM ፣ እና S2S 2ተኛ ዙር እንዲሁም H2R ሞጅል የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በአዳማ እና በሀዋሳ ከተማ መሰጠቱን ቀጥሏል፡፡ የሲስተም ስልጠናዉ በሚፈለገዉ አግባብ እና በቀላሉ እየተሰጠ እንደሚገኝ የንብረት አስተዳደር ወይም የ S2S ሞጅል […]
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት ከነበረዉ አሰራር ወደ ERP አሰራር ሲገባ ክፍተት እንዳይኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በአገልግሎቱ አዳራሽ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም ዉይይት የተደረገ ሲሆን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል። የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ እንዳሉት ተቋሙ አሰራሩን በሚያዘምንበት ወቅት ባለድርሻ አካላት የግብዓት ቆጠራ ላይ የአቅም ግንባታና የግብዓት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸዉ ጠቁመዋል። አገልግሎቱ […]