የኤጀንሲው የስነምግባር መመሪያ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በይፋ መመረቁን ስነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉሠው አያልነህ የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡የመመሪያው አስፈላጊነት ሕግንና ስርዓትን ለማስከበር፣ የሠራተኛን መብትና ግዴታን ለማስጠበቅ፣ መልካም አፈፃፀም ያላቸው ሠራተኞችን ለመለየትና መልካም ስነምግባርን ለማበረታታት እንደሆነ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ በኤጀንሲው አንዳንድ የስነምግባር እንደራስ ንብረት አለማየት፣ የሃብትና ንብረት አጠቃቀም ብክነቶችና የስራ ሠዓትን አለማክበር […]