የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 13 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን ሊያስከትብ የሚችል የክትባት መድኃኒቶችን አሰራጨ፡፡ ኤጀንሲው 11 አይነት የክትባት መድኃኒቶችን በዘመቻ እና ከጤና ተቋማቱ በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት ያሰራጨ ሲሆን ክትባቶቹ የፖሊዮ፣ የሳምባ ነቀርሳ፣ የሳምባ ምች፣ የጸረ አምስት፣የኩፍኝ፣ የቲታነስ፣ እና የተቅማጥ በሽታ እንዲሁም ክትባቱን ለመስጠት የሚያገለግሉ ሌሎች ተያያዥ ግብዓቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የክትባት መድኃኒቶችን ለቅድመ መከላከል የሚሰጡ ሲሆኑ ከ1.8 […]