Direct relief ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በድጋፍ የተገኙ 86 አይነት የተለያየ መጠን ያላቸው መድኃቶች እና የህክምና ግብዓቶች ለትግራይ ክልል የተሠራጩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

June 15, 2021News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ Direct relief ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በድጋፍ የተገኙትን የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ለትግራይ ክልል ማሰራጨቱን የመጋዘን አያያዝና ክምችት ባለሞያ ወ/ሪት ኑሀሚን ኤልያስ ሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ገልፀዋል ፡፡ስርጭቱ በመቀሌ የኤጀንሲው ቅርንጫፍ አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን 86 አይነት የተለያየ መጠን ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች መሆናቸውን ባለሞያዋ ገልጸዋል፡፡