ERP የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ከመሆኑም በላይ ለመድኃኒት አቅርቦት ሠንሠለት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጠንካራ የመረጃ ስርዓት እንዲኖር የ ERP ፕሮጀክትን በተለያዩ ምዕራፎች እንዲተገበር እየሰራ ሲሆን ከአሁን በፊት በተቆራረጠ መልኩ ሲተገበር የነበረውን የመረጃ ፍሰት ወደ ተቀናጀ እና እርስ በርስ የሚናበብ የመረጃ ስርዓት በመሆኑ ለመድኃት አቅርቦት ሠንሠለቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳሚኖረው የአገልግሎቱ የፋይናንስ እና የጤና ስርዓት ማጠናከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ ገለፁ፡፡ም/ዋ ዳይሬክተሩ በ change management ወርክሾፕ ላይ እንደገለጹት ተቋሙ ከነበርንበት የአሰራር ስርዓት ወደ አዲሱ አሰራር ሲገባ ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦችን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ተከታታይ በሆኑ መድረኮች ግንዛቤ በመፍጠር ለውጡን በአግባቡ መምራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡አክለውም ERP ውጤታማ የሚሆነው ሶፍትዌሩን ከማበልጸግ ባሻገር ሰራኞች አዲሱን አሰራር በደንብ ማወቅ እና መጠቀም ሲችሉ ነው፡፡ ስለሆነም ተቋሙን ትራንስፎርም የሚደርግ ፕሮጀክት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ቁርጠኛ መሆንን ይጠይቃል፡፡ በተመሳሳይ ከሰራተኞች በኩል የሚነሱ ጉዳዬችን በአግባቡ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የ ERP ፕሮጀክት የተለያዩ ደረጃዎችን አልፎ በግዥ ሂደት ላይ መሆኑ እና ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲተገበር ለአቅርቦት ሰንሰለቱ ደጋፊ የሆኑ አሰራሮችን ያቀናጃል ፣ ወጥ የሆነ አሰራር ይፈጥራል ፣ ትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርተን ውሳኔ እንድንሰጥ ያደርጋል ሲሉ የተናገሩት የፕሮጀክቱ ማኔጀር ወ/ሮ መንፈሴ ታደሰ ናቸው፡፡በዚህም የ ERP ትግበራውን የሚያሳልጡ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ፎካል ሆነው የሚሰሩ በየዳይሬክቶሬቱ እና በየቅርንጫፉ (change management Champion) መመረጣቸውን ጠቁመው እነዚህም የፕሮጀክት አካል ሆነው የሚሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ ለውጡን እንዲገነዘቡ እና እንዲመሩ ለማድረግ ዳይሬክቶሬቶች፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና በዳይሬክቶሬቱ እና በየቅርንጫፎቹ የተመረጡ ባለሙያዎች በ change management ዙሪያ አራት ተከታታይ ወርክሾፕ ተካሂዷል፡፡ እነዚህ ወርክሾፖች change management strategy ለማዘጋጀት በግብዓትነት ለመጠቀም እንደሆነ ገልጸው በቀጣይ የተለያዩ ወርክሾፖችና ስልጠናዎች የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ለፋይናንስ፣ ለሰው ሃብት አስተዳደር፣ ለመድኃኒት ክምችትና ስርጭት ቁልፍ ተግባሮች ጠቀሜታው የላቀ መሆኑና በግሎባል ፈንድ ድጋፍ እንደተደረገበት እና Deloitte በተባለ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባለው ድርጅት የማማከር ስራ እየተሰራ መሆኑን ከወ/ሮ መንፈሴ ማብራሪያ ማወቅ ተችሏል፡፡ከERP ፕሮጀክት ስራ ላይ የማይጠቀም የስራ ክፍል የለም የተባለ ሲሆን በተለይም መረጃን በማዕከል እንዲመጣ ያደርጋል ተብሏል፡፡ ይህም በመሆኑ ትክለኛው ምርት/መድኃኒት በትክክለኛው ጊዜ እና ቦታ ለማሰራጨት ይጠቅማል በተጨማሪ ERP ሲታሰብ ትክክለኛ ዳታ እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ የደንበኞች ትዕዛዝ በማዕከል ደረጃ እንዲሆን ያደርጋል ነው የተባለው፡፡
አወል ሀሰን