ERP/SMILE የተባለውን ትልቅ ፕሮጀግት ለመተግበር የተቋሙ ሰራተኞች ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
፨የዋናው መሥሪያ ቤት እና በሁሉም ቅርጫፍ ሠራተኞች በዙም በተደረገ ውይይት ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሄዷል።
፨በERP ሶፍት ዌር በመታገዝ መድሃኒት የማቅረብ ስራን የምናቃልበት ቴክኖሎ ቢሆንም የተቋሙ ሠራተኛች የማይተካ ሚና አላቸው።
፨የሶፍት ዌር ግዡ ያለቀ ቢሆንም ስራውን ሊሸከም የሚችሉ ኮምፒውተሮች ፣ሰርቨር እና የመሠረተ ልማት ስራዎች በግዥ በሂደት ላይ ናቸው።
፨ERP ከላይ አስከታች የተቀናጀ የመረጃ ስርአት ሲሆን ለ 10 አመት የአቅርቦት ሰንሠለቱ የመራበት ከነበረው HCMIS እና በማንዋል ሲሠሩ የነበሩትን ወደ አዲሱ ሰረአት ERP የሚኖረው የዳታ ሽግግር ከፍተኛ ተኩረት የሚሻ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።
፨በአቅርቦት እቅድ፣በመድሀኒት ግዝ፣በፋይናንስ ፣ተሽከርካሪዎች ስምሪት እና ጥገና፣ በክምችት ፣በቆጠራ ፣በጠቅላላ አገልግሎት እና በሰው ሀብት ልማት በተዘጋጁ ሞጁሎች ታግዞ ሶፍት ዌሩ የሚተገበር ሲሆን በጠራ መረጃ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል።
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ የአገልግሎቱን ራዕይ ለማሣካት ትልቅ አቅም እንደሚጠይቅ ሠራተኞች ዋንኛ የለውጥ መሪዎች ስለሆኑ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አክለውም ለውጥ ትግል እንዳለውና አገልግሎቱን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ለማድረስ በጋራ ከሠራተኛው ጋር ልንሠራና እኛ ታግለንና ተለውጠን ተቋሙን ልንለውጥ ይገባል ብለዋል።
ERP የአገልግሎቱን የተበታተነ አጠቃላይ መረጃ በአንድ ቋት በመሠብሠብ መረጃዎችን በቀላሉ እንድንቀባበልና የአገልግሎቱን አሠራር፣ የመድኃኒት አቅርቦቱን የሚያሻሽል ስርአት ነው።
ተግባራዊ ሲደረግም የአገልግሎቱን 57% አዳዲስ አሠራርን የሚተገብር፣ 30% የሚያስተካክልና 11 % የሚያስወግድ ሲሆን 71% አውቶሜትድ 25 % ሀገር አቀፍ አውቶሜትድ 4% በማኑዋል እንዲሠራ ያደርጋል።