ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያሳትፍ ውይይት ይካሔዳል ተባለ
July 16, 2019ፊውቸርድ ዜና
ከነሐሴ 8-10 /2011ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ኤጀንሲው ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እንደሚያካሒድ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቃልኪዳን ላቀው ለዝግጅት ክፍሉ ተናገሩ፡፡
በምክክር መድረክ ላይ ከለጋሽ አካላት፣ ከመድኃኒት አቅራቢዎች፣ ከኤጀንሲው ደንበኞችና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር የመድኃኒት አቅርቦት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ሰኔ 11 ቀን በነበራቸው ቃለ መጠይቅ አስታውቀዋል፡፡
በመድረኩ ኤጀንሲው እየተገበራቸው ባሉ የልህቀት ማዕከል፣ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት የካይዘን አተገባበር ላይ ለመወያየት ታቅዷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ቃልኪዳን የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እንደሚገመገም እና የ2012 በጀት ዓመት እቅድ ክለሳ በመድረኩ ለማድረግ እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡
ከምክክር መድረክ የተሻለ ተግባቦት በመፍጠር በህብረት ለመሥራት የሚያስችል አንድነት የመፍጠር እና በተቋማት መካከል ጣት የመጠቋቆም ችግርን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ከጤና ጣቢያዎች ባለድርሻ አካላት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ዶ/ር ቃልኪዳን ለዝግጅት ክፍሉ አስታውቀዋል፡፡